Daily Weather Report 24 Dec 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ምዕራብ ጎጃም፣ ምዕራብ ወለጋ እና ኢሉባቦር ዞኖች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቻግኒ፣ አርጆ፣ ጎሬ እና ደምቢ ዶሎ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በጋምቤላ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡
Yesterday, West Gojam, West Wollega and Ilubabor zones had cloud cover. In this regard, Chagni, Arjo, Gore and Dembi Dolo received light to moderate rainfall while Gambella recorded heavy rainfall. On the other hand, dry, sunny and windy summer weather has been observed in the northeast, east and central regions of our country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል።
Tomorrow there will be cloud cover over the western parts of the country. Along with this, Ilubabor and Kelem Welega zones from the Oromia region; The Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones of South West Ethiopia region and Majang and Anuwak zones of Gambella region will receive light rainfall. On the other hand, the northeast, east and central regions of our country will have dry, sunny and windy weather.