Daily Weather Report 24 Dec 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ጅማ፣ ከፋ ዞኖች የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆንና በደባርቅ፣ ላይበር፣ ጋቲራ እና ቴፒ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሐሮማያ፣ ጅግጅጋ፣ አርሲ ሮቤ እና በባሌ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, North Gondar, West Gojam, Jimma, Kefa zones had cloud cover and light to moderate rains were recorded in Debark, Leiber, Gatira and Tepi. On the other hand, the northeast, east and central parts of our country had dry, sunny and windy summers. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded as below 5oC in Haromaya, Jigjiga, Arsi Robe and Bale Robe.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ እንደሚስተዋልባቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow there will be cloud cover over the western parts of the country. Along with this, Ilubabor, West and Kelem Welega zones from the Oromia region; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones of South West Ethiopia region and Majang and Anuwak zones of Gambella region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). On the other hand, numerical forecast indicate that dry, sunny and windy weather will be observed in the northeast, east and central areas of our country.