Daily Weather Report 24 Aug 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንታ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ስልጤ እና ጉራጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፍቼ፣ በሻምቡ፣ በባሌሮቤ እና በጂንካ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, north west, west, north east, central, south and east parts of our country had cloud coverage and accumulation. In association with this, the south and southeast Tigray zones; north and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo special zone and north Shewa zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Horo Guduru Wellega, west and east Wellega, Buno Bedele, north, west, south west and east Shewa, Bale, Arsi, west Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the Benshangul Gumuz region Metekel zone; from the southwest Ethiopia region Konta zone; from the central Ethiopia Hadiya, Silte and Gurage zones; from the south Ethiopia region Gamo, Gofa and south Omo Zones and Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Fiche, Shambu, Balerobe and Jinka.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ቄላም ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ እና ሀድያ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀለምት፣ በደባርቅ፣ በአርማቾ፣ በጃዊ፣ በፓዌ፣ በባህርዳር ዙሪያ፣ በቡለን፣ በካማሽ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በጊዳአያና፣ በክራሙ፣ በሐሮሊሙ፣ በሳሲጋ እና በሲቡሲሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud coverage and accumulation over the Kiremt rainfall benefiting of the western half, central, northeastern and eastern parts of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra Zones; from the Benshangul Gumuz region, Asossa, Kamash, Metekel and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Kelam Wellega, Horo Guduru Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Bale, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba and Hadiya zones and Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Tselemt, Debark, Armacho, Jawi, Pawe, Bahirdar Zuria, Bulen, Kamash, Nedjo, Gimbi, Gidayana, Kiramu, Harolimu, Sasiga and Sibusire will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.