Daily Weather Report 24 Aug 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ)፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዳሊፋጊ፣ በላንጌ እና በሻምቡ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, northwest, west, northeast, south and eastern parts of the country had cloud coverage and accumulation. In this regard, the north west, central, south east and east Tigray zones; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo special zone and north Shewa zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Oromia region Jimma, Horo Guduru Wellega, west and east Wellega, Buno Bedele, north Shewa (Salale), Bale, west and east Harerge zones; Addis Ababa; Harar; from Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the south Ethiopia region Gamo, Gofa, Wolaita and Gedeo zones and from the south west Ethiopia region Sheka zone received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Dalifagi, Lange and Shambu.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ቄላም ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በወንበራ፣ በደምቢ፣ በካማሽ፣ በጅማ አርጆ፣ በባኮጢቤ፣ በሚዳኬኝ፣ በጨዋቃ፣ በቦረቻ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በኤጀሬ፣ በኢሉ እና በቀወት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በጋሞ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ኦሞ፣ ቦረና እና ከሶማሌ ክልል የኤረር፣ ጃራር፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ አፍዴር እና ዳዋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the coming day, the weather conditions favourable for the formation of Kiremt rains will continue over Kiremt benefit parts of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Gabi, Fanti, Awusi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region, Asossa, Kamash, Metekel and Mao Komo and zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Kelam Wellega, Horo Guduru Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Wanbera, Dembi, Kamash, Jimma Arjo, Bako Tibe, Midakegn, Chewaka, Borecha, Nedjo, Gimbi, Ejere, Ilu and Kewet will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, Gamo, south and west Omo, Borena and from Somali region Erer, Jarar, Korahe, Shebelle Afder and Dawa zones will receive light to moderate rainfall at a few places.