Daily Weather Report 24 Aug 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኑዌር ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎንደር እና በፓዌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the northwest, northeast, west, south and east parts of the country. In line with this, the northwest, central, south, southeast and east Tigray zones, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo Ethnic Special Zone and north Shewa zones; Jimma, Horo Guduru, west Wellega, Buno Bedele, east Shewa, Arsi, west Hararge, Borena and East Borena zones; from Gambella region Nuer zone; from Benishangul-Gumuz region Metekel and Assosa zones and from Southern Ethiopia region Gofa zone received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy amounts of more than 30 mm were recorded in Gondar and Pawe.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄላም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በወረኢሉ፣ በአንጎለላ፣ በቀወት፣ በቅምቢቢት፣ በኦሞ፣ በአርሲነገሌ፣ በኮፈሌ፣ በዶዶላ፣ በአዳባ፣ በአሴኮ፣ በየኪ፣ በማሻ፣ በሸካ፣ በጎደሬ፣ በቸታ፣ በኮንታ፣ በተርጫ፣ በጎምቦራ፣ በሌሞ፣ በሳንኩራ፣ በካቻብራ፣ በባዳዋቾ፣ በወራ፣ በዳሞትሶሬ፣ በካዎኮይሻ፣ በክንዶኮይሻ፣ በሁምቦ፣ በቦረዳ፣ በብላቴ፣ በደራራ፣ በጭሬ እና በአሮሬሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud coverage and accumulation over the Kiremt rainfall benefiting parts of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west Wellega, Horo Guduru Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from south Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Derashe, Amaro, Burji, Konso and south Omo zones; all zones of Sidama region and from the Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Wareilu, Angolela, Kewat, Kimbibit, Omo, Arsinegele, Kofele, Dodola, Adaba, Aseko, Yeki, Masha, Sheka, Godere, Cheta, Konta, Tercha, Gombora, Lemmo, Sankura, Kachabira, Badawacho, Warra, Damotsore, Kawokoisha, Kindokoisha, Humbo, Boreda, Bilate, Derara, Chire and Aroresa will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events the south and southeast parts of the country will receive light to moderate rainfall.