Daily Weather Report 24 Aug 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ፋንቲ፣ እና አዉሲ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ጉራጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈንና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በስንቃጣ፣ በቻግኒ፣ በየትኖራ፣ በመካነ ሰላም፣ በባቲ፣ በጉንዶመስቀል እና በሻምቡ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In association with this, the north west, central, south, south east and east Tigray zones; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo and north Shewa zones; from the Afar region Gabi, Fanti, and Awusi zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, north, west and south west Shewa, Arsi, Bale, west and east Hararge, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Agnuak zone from Gambella region; from the Benshangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the south west Ethiopia region Sheka Zone; from the central Ethiopia region Hadiya and Gurage zones; from the south Ethiopia region Wolaita zone; Sidama region zones and Somali region Fafen and Liban zones received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Sinkata, Chagni, Yetnora, Mekane Salam, Bati, Gundomeskel and Shambu.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ካማሽ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሽራሮ፣ በፀለምት፣ በዕብናት፣ በፎገራ፣ በላይጋይንት፣ በኤሊዳር፣ በአሳይታ፣ በዝቋላ፣ በሰቆጣ፣ በቡግና፣ በዳዉንት፣ በሳይንት፣ በደሴ ዙሪያ፣ በየም ልዩ ዞን፣ በጊቤ፣ በአዳሚ ቱሉ፤ ጂዶ ኮምቦልቻ፣ በአሌ፣ እና በደዴሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will continue over Kiremt benefit parts of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hari zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel, Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Kamash and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Derashe, Amaro, Burji, Konso and south Omo zones; all zones of Sidama region and Siti zone of Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Shiraro, Tselemt, Ebnat, Fogera, Laigaint, Elidar, Asayita, Zikuala, Sekota, Bugna, Dawunt, Saint, Desie Zuria, Yem special zone, Gibe, Adama Tullu; Jido Kombolcha, Alle and Dedesa will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events the south and southeast parts of the country will receive light to moderate rainfall.