Daily Weather Report 24 Aug 26

Weather Summary for previous day

Aug. 25, 2024

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በትግራይ፤ በአማራ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሰሜን ሶማሌ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ ዞን፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በባህርዳር፣ በአየሁ፣ በነቀምቴ፣ በኢጃጂ፣ በቡሬ፣ በአለምተፈሪ፣ በአንገርጉትን፣ በጋምቤላ እና በአዲስ አበባ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the Kiremt rainfall benefiting regions Tigray, Amhara, Benishangul-Gumuz, Oromia, Gambella, Afar, northern Somali and southwestern Ethiopia were strong cloud cover and accumulation. In association with this, northwest, central, south, southeast and east Tigray Zones, north, central and south Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Awsi zone, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horogudru Wellega, west, east, north and southwest Shewa, west Hararge, Addis Ababa; from Gambella region Agnuwak zone; from Southwest Ethiopia region Sheka and Bench Sheko zones, Sidama regional zones and from Somali region Siti zone received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Bahir Dar, Ayehu, Nekemte, Ejaji, Bure, Alem Teferi, Anger Gutin, Gambella and Addis Ababa.

Weather Forecast for next day

Aug. 27, 2024

በነገው ዕለት ወደ ሀገራችን የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አከባቢዎች ላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ፈንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቄላም ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በታህታይ አዲያቦ፣ በኦፍላ፣ በራያ አለማጣ፣ በጨርጨር፣ በቃፍታ ሁመራ፣ በማይካድራ፣ በመተማ፣ በምዕራብ አርማጭሆ፣ በምስራቅ በለሳ፣ በእብናት፣ በስማዳ፣ በእነማይ፣ በሰናን፣ በጎዛመን፣ በደምበጫ፣ በዝቋላ፣ በሰቆጣ፣ በጊዳን፣ በጋዞ፣ በሳይንት፣ በለጋምቦ፣ በጅሌጥሙጋ፣ በአንጾኪያ፣ በኤፍራታናግድም፣ በሞረትናጅሩ፣ በቀወት፣ በጭፍራ፣ በጊምቢ፣ በቤጊ እና በጊዳሚ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ሐረርጌ፤ ሐረር እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ እና ቆራሄ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the moist air entering to our country will continue to intensify over the Kiremt rain-benefiting areas of the country. In line with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; from Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region: Kelbetti, Gabi, Fenti, Awusi and Hari zones; from Oromia region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Kelam Wellega, Horogudru Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Hararge zones: Addis Ababa, Dire Dawa; Benishangul-Gumuz region: Metekel, Assossa, Mao Como and Kamash zones; from Gambella region Anuak, Itang and Majang zones; from southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Kefa zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; from Southern Ethiopia region Wolayta and Gedeo zones; Sidama region and from Somali region Siti zone will receive light to moderate amounts of rainfall in many places. In addition, Tahtai Adiabo, Ofla, Raya Alemta, Chercher, Kafta Humera, Maikedra, Metema, west Armachiho, east Belesa, Ebint, Simada, Enemay, Senan, Guzamen, Dembecha, Zqala, Sekota, Gidan, Gazo, Sayint, Legambo, Jile Tumuga, Antsokiya, Efiratan Gidem, Moretna Jiru, Kewot, Chifra, Gimbi, Begi and Gidami will receive heavy amounts of rain in 24 hours. On the other hand, based on the intensifying weather events, west Omo, Dauro, Konta, Gofa, Gamo, Basketo, Bale and east Bale, Borena and east Borna, west Hararge, Harar and from Somali region Fafen, Dawa, Liben, Afder, Shebelle and Korahe zones will receive light to moderate amounts of rain in a few places.