Daily Weather Report 24 Aug 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳዉሮ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ኮንሶ፣ ጌዲኦ፣ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ ዞን እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአጽቢ፣ በአዲግራት፣ በስንቃጣ (ፍሬወይኒ)፣ በሽሬ፣ በመቀሌ፣ በማይጨው፣ በአይደር፣ በደባርቅ፣ በጎንደር፣ በላሊበላ፣ በነፋስ መውጫ፣ በወገልጤና እና በኢጃጅ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting areas of the country had strong cloud coverage and accumulation. In this regard, the northwest, central, eastern, south and southeast Tigray zones; from Amhara region west, north and central Gondar, east and west Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelem Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Guj and west Guji, Borena and east Borena, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa, Harar; from Benishangul-Gumuz region Assosa and Metekel zones; Southwest Ethiopia region Dauro zone; from Central Ethiopia region Hadia, Gurage and Silte zones; from South Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Konso, Gedeo, Burji and South Omo zones, Sidama regional zones; from Gambella region Agnwak zone, and from Somali region Fafen zone received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Atsebi, Adigrat, Sinkata (Freweini), Shire, Mekelle, Maichew, Aider, Debark, Gondar, Lalibela, Nefasmewicha, Wogltena and Ejaji.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲና ፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጭፍራ፣ በአሳይታ፣ በቆቦ፣ በጉባላፍቶ፣ በደሴ፣ በዋድላ፣ በአንጾኪያ፣ በቀወት፣ በምንጃርሸንኮራ፣ በቦሴቲ እና በዶዶታ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow there will be strong and widespread cloud cover and accumulation over the Kiremt benefiting areas of the northern, west, northeastern, central, southern and eastern parts of the country. In association with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; from Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wello, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awsi and Hari zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assossa, Maokomo and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east Wellga, Horogudru Wellga, southwest, east, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Bale, Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa, Dire Dawa, Harar; from Gambella region Agnuak and Majang zones; from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Fafa, Konta and Dauro zones; from Central Ethiopia region: from Central Ethiopia Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Amaro and Gedeo zones; all zones of the Sidama region and from Somali region Siti and Fafen zone will receive light to moderate amounts of rainfall in many of their places. In addition, in Chifra, Asaita, Kobo, Gubalafto, Dessie, Wadla, Antsokiya, Kewet, Menjarsugarkora, Boseti and Dodota will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.