Daily Weather Report 24 Aug 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄላም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአለምከተማ፣ በነጆ፣ በደንብዶሎ፣ በአርጆ፣ በቡሬ፣ በአንገርጉትን፣ በወሊሶ፣ በማሻ፣ በአማን፣ በእንድብር እና በጂጂጋ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In this regard, the northwest, central, south and southeast Tigray zones; north and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Awusi zone from Afar region; Asosa zone from Benishangul Gumuz region; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, West, south west and east Shewa, west Guji, Borena and east Borena, Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the Benishangul Gumuz region Metekel zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the central Ethiopian region of Hadiya, Gurage and Silte zones; from the south Ethiopia region Gofa, Gamo, Burji and south Omo zones; Sidama region zones and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Alemketama, Nedjo, Denbidollo, Arjo, Bure, Angergutin, Waliso, Masha, Aman, Indibir and Jijiga.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአብዓላ፣ በዳሎል፣ በአፍዴራ፣ በኤሊዳር፣ በአሳይታ፣ በበራሕሌ፣ በቆቦ፣ በጉባላፍቶ፣ በመቅደላ፣ በደሴ፣ በከለላ፣ በወግድ፣ በወረኢሉ፣ በአንጾኪያ፣ በቀወት፣ በምንጃርሸንኮራ በአዳአ፣ በአዋሽፋንታሌ እና በጋብላሉ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ደቡብ ኦሞ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be strong and widespread cloud coverage and accumulation over the Kiremt rain benefiting areas of the north, west, northeast, central, south and east parts of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hari zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel, Asossa and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east Wellega, Horo Guduru Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Amaro and Gedeo zones; all zones of Sidama region and from the Somali region Siti zone will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Abiala, Dalol, Afdera, Elidar, Asayita, Berahile, Kobo, Gubalafto, Mekdella, Desie, Kelela, Wegdi, Were Iluu, Antsokia, Kewat, Minjarshenkora, Ada’a, Awashfantale and Gablalu will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events south Omo and west Omo zones will receive light rainfall.