Daily Weather Report 24 Aug 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና መተከል ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአፅቢ፣ በሲሪንቃ፣ በወገልጤና፣ በጭፍራ፣ በእነዋሪ፣ በየትኖራ፣ በፍቼ፤ በነቀምቴ፣ በአርጆ፣ በአይራ፣ በጂንካ፣ በግራዋ እና በቁሉቢ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In association with this, the northwest, central, south and southeast Tigray zones; north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Awusi zone from the Afar region; from the Benishangul Gumuz region Asossa and Metekel zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, west Guji, Borena, Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the central Ethiopian region Hadiya, Gurage and Silte zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo and south Omo Zones; Sidama region Zones and from Somali region Fafen and Korahe zones received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Atsebi, Sirinka, Wegeltena, Chifra, Enewari, Yetnora, Fiche, Nekemte, Arjo, Aira, Jinka, Girawa and Kulubi.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ቆራሔ፣ ኤሬር፣ ሸበሌ እና ኖጎብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአፅቢ፣ በአበርገሌ፣ በሳሓርቲሳም፤ በአላማጣ፣ በጨርጨር፣ በአብዓላ፣ በዳሎል፣ በጭፍራ፣ በአዉራ፣ በዳሊፋጊ፣ በኤሊዳር፣ በአሳይታ፣ በላስታ፣ በዳዉንት፣ በመቅደላ፣ በከለላ፣ በወግዲ፣ በስማዳ፣ በእነማይ፣ በሞጣ፣ በጎዛመን፣ በደንበጫ፣ በአንካሻ፣ በቡለን፣ በማኦ ኮሞ፣ በካማሽ፣ በጋምቤላ፣ በዲማ፣ በጊዳሚ፣ በሲቡሲሬ፣ በዲጋ፣ በጉቶጊዳ፣ በባኮ፣ በኖኖ፣ በኤጀሬ፣ በወንጪ፣ በቶሌ፣ በአዳአ፣ በጊምቢቹ፣ በጮሌ፣ በአንቻር፣ በድሬዳዋ፣ በሐሮማያ፣ በመቱ፣ በበደሌ፣ በሊሙሴቃ፣ በየኪ፣ በሸካ፣ በቸና እና በማጂ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከሚጠናከሩት የደመና ክምችቶች በመነሳት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the weather conditions favourable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the areas that benefit from Kiremt rains. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Derashe, Amaro, south Omo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and from the Somali region of Siti, Fafen, Jarar, Korahe, Erer, Shebelle and Nogob zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Atsibi, Abergele, Sahartisamri, Alamata, Chercher, Abiala, Dalol, Chifra, Awuraa, Dalifagi, Elidar, Asayita, Lasta, Dawunt, Mekdella, Kelela, Wegdi, Simada, Enemay, Motta, Gozaman, Denbecha, Ankasha, Bulen, Mao Komo, Kamash, Gambella, Dima, Gidami, Sibusire, Digga, Gutogida, Bako, Nono, Ejere, Wenchi, Tole, Ada’a, Gimbichu, Chole, Anchar, Dire Dawa, Haromaya, Mettu, Bedele, Limuseka, Yeki, Sheka, Chena and Maji will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the south and southeast parts of the country will receive light to moderate rain due to the strengthening of accumulation clouds.