Daily Weather Report 24 Aug 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞን፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳውሮ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በተጨማሪም በቡለን፣ በደብረብርሀን፣ በሳውላ እና በወላይታ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the Kiremt rain-benefiting areas of the northwest, west, Central, northeast, east and Southerner parts of the country. In association with this, the south east Tigray zone; from Amhara region north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel zone; from Oromiya region Jimma, east Wellga, Guji and west Guji, west and east Harerge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from Southwest Ethiopia region zones Dauro zone; from Central Ethiopia region Gurage and Silte zones; from Southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Gedeo and south Omo zones received light to moderate amounts of rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Bullen, Debre Birhan, Sawla and Wolayta.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጅ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዲኦ እና አማሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአለፋ ጣቁሳ፣ ጭልጋ፣ በላይጋይንት፣ በደሀና፣ በቡግና፣ በሀገረማርያም፣ በዳንግላ፣ በማኦኮሞ፣ በሊሙ፣ በኢባቱ፣ በግንደበረት፣ በኮቢ፣ በጀልዱ፣ በጊዳኒ፣ በአንፊሎ፣ በሶኮሩ፣ በሊሙቆሳ፣ በቀርሳ፣ በየም ልዩ ወረዳ፣ በአሜካ፣ በጊቤ፣ በሶሮ፣ በጨሃ፣ በቦራ፣ በዶዶታ፣ በአዳአ፣ በሲሬ፣ በጢዮ፣ በሙኒሳ፣ በጀጁ፣ በአርሲ በገሌ፣ በኮፈሌ፣ በኮሬ፣ በአዳባ፣ በአጋርፋ፣ በዲሾ እና በሀዋሳ ዙሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ፣ በደራሼ፣ በአሌ እና ከሶማሌ ክልል የጃራር፣ ኤረር እና ዶሎ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the coming day, the weather conditions favourable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the areas benefiting from Kiremt rains. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benishangul Gumuz region Asossa, Mao Komo, Metekel and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones From South Ethiopia region, Wolayta zone; all zones of Sidama region and from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate amount of rainfall in many places. In addition, In addition, Alfa Takusa, Chilga, Lay Gayint, Dehana, Bugna, Hager Mariam, Dangla, Mao Komo, Limu, Ibatu, Gundebret, Cobi, Jeldu, Gidani, Anfilo, Sokoru, Limukosa, Kersa, Yem Special District, Ameka, Gibe, Soro, Cheha, Bora, Dodota, Adaa, Sire, Tiyo, Munisa, Jeju, Arsi Negele, Kofele, Kore, Adaba, Agarfa, Dinsho and Hawassa zuria will receive heavy amounts of rain in 24 hours. On the other hand, in South Ethiopia region south Omo, Derashe and Alle and from Somali region Jarrar, Erer, and Doolo zones will have light amounts of rainfall in a few places.