Daily Weather Report 24 Aug 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የትግራይ፤ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ኦሮሚያ፤ አፋር፤ ደቡብ ምዕራብ ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ጌዲኦ እና ኮንሶ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጽጽቃ እና በላንጌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the Kiremt rain-benefiting areas of Tigray, Amhara, Benishangul-Gumuz, Oromia, Afar, Southwest, Central and Southern Ethiopia. In connection with this, the northwest, central, south, southeast and east Tigray zones; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Awsi zone of Afar region; from Benishangul-Gumuz region Metekel zone; Jimma, Ilubabor, Buno Bedle, east Wellga, north, west, southwest and east Shewa, Arsi, Bale, Borena, Guji and west Guji, west and east Harerge zones; Addis Ababa; from Southwest Ethiopia region zones Bench Sheko, Sheka and Dauro: from Central Ethiopia region Hadia, Gurage and Silte zones;from Southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Gedeo and Konso zones received light to moderate amounts of rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Tsitsika and Lange.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀለምት፣ በኢገሌ፣ በጨርጨር፣ በራያ አላማጣ፣ በአብዓላ፣ ያሎ፣ አርጎባ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ በላይጋይንት፣ በስማዳ፣ በእስቴ፣ በሰቆጣ፣ በደሀና፣ በጋዝግብላ፣ በላስታ፣ በዳዉንት፣ በአንጎት፣ በዋድላ፣ በመቅደላ፣ በከለላ፣ በወግዲ፣ በበረኽት፣ በአረርቲ፣ በሀገረማርያም፣ በሁለትጁነሴ፣ በእነብሴ ሳርምድር፣ በእናርጅ እናውጋው፣ በደጋዳሞት፣ በጎንጅ፣ በሊሙ፣ በአርጆ፣ በኑኑ ኩምቢ፣ በሊሙ ሰቃ፣ በዳኖ፣ በኖኖ፣ በባኮ፣ በአመያ፣ በወንጭ፣ በአዲስ አበባ፣ በአሌልቱ፣ በቅምቢብቲ፣ በጂዳ፣ በአዳአ፣ በጊምቢቾ፣ በሲሬ፣ በመርቲ፣ በአሴኮ እና በዶዶታ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲኦ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ከሶማሌ ክልል የጃራር፣ ኤረር፣ ሊበን፣ ዳዋ እና አፍዴር ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the coming day, the weather conditions favourable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the areas benefiting from Kiremt rains. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benishangul Gumuz region Asossa, Metekel and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones From South Ethiopia region, Wolayta zone; all zones of Sidama region and from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate amount of rainfall in many places. In addition, In addition, in Tselemt, Egele, Chercher, Raya Alamata, Abala, Yalo, Argoba, Awash Fentale, Laiy Gayint, Simada, Esite, Sekota, Dehana, Gazbla, Lasta, Dawunt, Angot, Wadla, Mekdela, Kelela, Wegdi, Berekht, Ararti, Hagermariam, HuletuJunese, Enebesse Sarmidr, Enarji Enawgaw, Degadamot, Gonj, Limu, Arjo, Nunu Kumbi, Limu Seka, Dano, Nono, Bako, Amaya, Wonchi, Addis Ababa, Aleltu, Kambibiti, Jida, Adaa, Gimbicho, Sire, Merti, Aseko and Dodota will receive heavy amounts of rain in 24 hours. On the other hand, in Gofa, Gamo, Basquet, South Omo, Gedeo, west Guji, Borena and from Somali region Jarrar, Erer, Liben, Dawa and Afder zones will have light amounts of rainfall in a few pleaces.