Daily Weather Report 24 Aug 16

Weather Summary for previous day

Aug. 15, 2024

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቻግኒ፣ በፍቼ፣ በኑራኤራ፣ በአማን፣ በወላይታ እና በዲላ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In association with this, the northwest, central, south, southeast and east Tigray zones; north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Afar region Awusi; from the Benshangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, west Omo and Dawuroo zones; from the central Ethiopian region Hadiya, Gurage and Silte zones; from the south Ethiopia region, Wolayta, Gofa, Gamo, south Omo and Konso zones and Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Chagni, Fiche, Nuraera, Aman, Wolaita and Dilla.

Weather Forecast for next day

Aug. 17, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ቆራሔ፣ እና ኖጎብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀለምት፣ በአድዋ፣ በአፅቢ፣ በሳሓርቲሳምረ፣ በእንደርታ፣ በአላማጣ፣ በጨርጨር፣ በአብዓላ፣ በጭፍራ፣ በአዉራ፣ በዳሊፋጊ፣ በኤሊዳር፣ በአሳይታ፣ በላይጋይንት፣ በስማዳ፣ በእነማይ፣ በሰቆጣ፣ በዝቋላ፣ በደሀና፣ በጋዝግብላ፣ በላስታ፣ በቆቦ፣ በጉባላፍቶ፣ በዳዉንት፣ በዋድላ፣ በመቅደላ፣ በከለላ፣ በወግዲ፣ በደሴ፣ በወረኢሉ፣ በባቲ፣ በጨፋ፣ በመራቤቴ፣ በሞረትናጅሩ፣ በአንጾኪያ፣ በበረኽት፣ በቀወት፣ በአንኮበር፣ በድሬዳዋ፣ በጋብላሉ፣ በማኦ ኮሞ፣ በካማሽ፣ በአኮቦ፣ በጋምቤላ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በአይራ፣ በሳሲጋ፣ በሲቡሲሬ፣ በጉቶጊዳ፣ በጨዋቃ፣ በበደሌ፣ በሰተማ፣ በሶኮሩ፣ በአቢቹኛዓ፣ በጂዳ፣ በኖኖ፣ በባኮ፣ በአመያ፣ በአዳአ፣ በአንቻር፣ በቀበና፣ በእዝሓ፣ በስልጤ፣ በለሞ፣ በጠምባሮ፣ በቤንች፣ በማጂ፣ በደቻ፣ በኮንታ፣ በተርጫ፣ በዳሞትሶሬ እና በብላቴ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be strong and widespread cloud coverage and accumulation over parts of the country that benefit from the Kiremt rains. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benshangul Gumuz region Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Derashe, Amaro, south Omo, Konso, Burji and Gedeo zones; all zones of the Sidama region and from the Somali region of Siti, Fafen, Jarar, Korahe, and Nogob zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Tselemt, Adwa, Atsebi, Sahartisamere, Enderta, Alamata, Chercher, Abiala, Chifra, Aura, Dalifagi, Elidar, Asayita, Laigaint, Simada, Enemay, Sekota, Zikuala, Dehana, Gazgebila, Lasta, Kobo, Gubalafto, Dawunt, Wadila, Mekdella, Kelela, Wegdi, Desie, Wareilu, Bati, Cheffa, Merabete, Moretinajru, Antsokia, Berehat, Kewat, Ankober, Dire Dawa, Gablalu, Mao Komo, Kamash, Akobo, Gambella, Nedjo, Gimbi, Aira, Sasiga, Sibusire Gutogida, Chewaka, Bedele, Setema, Sokoru, Abichugna, Jidda, Nono, Bako, Ameya, Ada’a, Anchar, Kebena, Izeha, Silte, Lemo, Tembaro, Bench, Maji, Decha, Konta, Tercha, Damotsore and Bilate will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.