Daily Weather Report 24 Aug 15

Weather Summary for previous day

Aug. 14, 2024

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የትግራይ፤ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ኦሮሚያ፤ አፋር፤ ደቡብ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጎፋ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማይጨው፣ በጎንደር፣ በደባርቅ፣ በፅፅቃ፣ በአልጌ እና በአልያ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the Kiremt rain-benefiting areas of Tigray, Amhara, Benishangul-Gumuz, Gambella, Oromia, Afar, Southwest, Central and Southern Ethiopia, as well as eastern parts of the country. In association with this, the northwest, central, south, southeast and east Tigray zones, north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Awsi zone; from Benishangul-Gumuz region, Metekel and Assosa zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellga, north, southwest and east Shewa, Arsi, Bale and east Hararge zones; Addis Ababa; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko and Sheka zones; from Central Ethiopia region Hadia, Gurage and Silte zones; from the Southern Ethiopia region Wolayta and Gofa zones, and Sidama regional zones received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Michew, Gondar, Debark, Tsitsika, Alge and Eliya.

Weather Forecast for next day

Aug. 16, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳንሻ፣ በሽሬ እንዳሥላሴ፣ በሽራሮ፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በሓውዜን፣ በአበርገሌ፣ በሳህርተሳምረ፣ በአፅቢ፣ በኦፍላ፣ በአላማጣ፣ በጨርጨር፣ በአብዓላ፣ በጭፍራ፣ በዳሊፋጊ፣ በቴሩ፣ በኤሊዳር፣ በአሳይታ፣ በሚሌ፣ በደባርቅ፣ በመተማ፣ በአርማጮ፣ በደምቢያ፣ በፎገራ፣ በፋርጣ፣ በላይጋይንት፣ በስማዳ፣ በጃዊ፣ በጉባ፣ በሜጫ፣ በሞጣ፣ በእነማይ፣ በሰቆጣ፣ በዝቋላ፣ በደሀና፣ በጋዝግብላ፣ በላስታ፣ በቆቦ፣ በጉባላፍቶ፣ በደላንታ፣ በዳዉንት፣ በዋድላ፣ በመቅደላ፣ በከለላ፣ በሳይንት፣ በወግዲ፣ በደሴ፣ በወረኢሉ፣ በባቲ፣ በጨፋ፣ በመራቤቴ፣ በሞረትናጅሩ፣ በአንጾኪያ፣ በበረኽት፣ በቀወት፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በሺኒሌ፣ በደምበል፣ በሊሙሴቃ፣ በሊሙቆሳ፣ በሶኮሩ፣ በአቢቹኛዓ፣ በደራ፣ በኖኖ፣ በጂባት፣ በጀልዱ፣ በወንጪ፣ በአመያ፣ በወሊሶ፣ በቶሌ፣ በቦራ፣ በቦሴቲ፣ በአሴኮ፣ በአንቻር፣ በሚኤሶ፣ የየም ልዩ ዞን፣ በቸሃ፣ በቀበና፣ በሶዶ፣ በእዝሓ፣ በሁምቦ፣ በካዎኮይሻ፣ በብላቴ፣ በሰሜን ቤንች እና በደቻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እየተስተዋለ ስለሆነ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲዩት ይጠቁማል፡፡

Tomorrow, the forecast information indicates that there will be strong and widespread cloud cover and accumulation over the Kiremt rain-benefiting areas of the country. In line with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; from Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo Ethnic Special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Kilbeti zones, Gabi, Fanti, Awsi and Hati zones; Benishangul-Gumuz region of Metekel, Assosa, Mao Como and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellga, Horogudru Wellega, Kelem Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji west Guji, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa, Dire Dawa, Harar; Gambella region: Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from the Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Derashe, Amaro, South Omo, Konso, Burji and Gedeo zones; all of Sidama region and from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate (1-29 mm) amounts of rain at many of their locations. In addition, in Dansha, Shire Endesilase, Shiraro, Adwa, Axum, Hauzen, Abergele, Sahrsamre, Atsbi, Ofla, Alamata, Chercher, Abala, Chifra, Dalifagi, Teru, Elidar, Asaita, Mille, Debark, Metema, Armacho, Dembia, Fogera, Farta, Lay Gayint, Simada , Jawi, Guba, Mecha, Motta, Enemay, Sekota, Zqala, Dehana, Gazbla, Lasta, Kobo, in Gubalafto, Delanta, Dawnit, Wadla, Mekidela, Kelela, Saint, Wegdi, Dessie, Wereilu, Bati, Cheffa, Merebete, Moretnajru, Antioch, Berehet, Kewote, Addis Ababa, Dire Dawa, Shinile, Dembel, Limuseka, Limukosa, Sokoru, Abichugna, Dera, Nono, Jibat, Jeldu, Wonchi, Amaya, Woliso, Tole, Bora, Bosetti, Asieko, Anchar, Miesso, Yem Special zone, Cheha, Kebena, Sodo, Ezha, Humbo, Kawokoisha, Bilate, north Bench and Decha will receive heavy amounts of rainfall of over 30 mm in 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute suggests that the community take the necessary precautions as frequent heavy rainfall is observed in different parts of the country.