Daily Weather Report 24 Aug 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የትግራይ፤ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ሰሜን ሶማሌ፤ ደቡብ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ፣ ፋንቲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ቡለን ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በመቀሌ፣ በደብረታቦር፣ በባህርዳር፣ በደብረማርቆስ፣ በኮምቦልቻ፣ በባቲ፣ በጨፋ፣ በወረኢሉ እና በእነዋሪ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting areas Tigray; Amhara; Benishangul Gumuz; Oromia, Afar, northern Somali; southwest, central and southern Ethiopia as well as eastern parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In association with this, the northwest, central, south, southeast and east Tigray zones; north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Afar region Awusi, Fanti and Gabi zones; from the Benishangul Gumuz region Asossa and Bulen zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, west, south west and east Shewa, west Guji, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko and Dawuro Zones; from the central Ethiopia region Hadiya and Silte zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Konso, Burji and South Omo zones and Sidama region zones receied light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Mekelle, Debretabor, Bahir Dar, Debre Markos, Combolcha, Bati, Chifra, Wereilu and Enewari.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሁመራ፣ በወልቃይት፣ በማይካድራ፣ በፀገደ፣ በዳንሻ፣ በሽሬ እንዳሥላሴ፣ በሽራሮ፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በአበርገሌ፣ በሳሓርቲሳምረ፣ በአፅቢ፣ በዳሊፋጊ፣ በጭፍራ፣ በዳሎል፣ በበራሀሌ፣ በአብዓላ፣ በደባርቅ፣ በመተማ፣ በፎገራ፣ በፋርታ፣ በላይጋይንት፣ በስማዳ፣ በፓዌ፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በቡለን፣ በዳንጉር፣ በወምበርማ፣ በሰከላ፣ በሜጫ፣ በሞጣ፣ በሰቆጣ፣ በዝቋላ፣ በላስታ፣ በዳዉንት፣ በዋድላ፣ በመቅደላ፣ በከለላ፣ በሳይንት፣ በወግድ፣ በደሴ፣ በመራቤቴ፣ በሞረትናጅሩ፣ በአንጾኪያ፣ በማኦ ኮሞ፣ በአሶሳ፣ በአቦቦ፣ በጆሬ፣ በጎግ፣ በዲማ፣ በአዲስ አበባ፣ በጊዳሚ፣ በጊዳ፣ በሲቡሲሬ፣ በደራ፣ በደገም፣ በጂዳ፣ በያያጉለሌ፣ በኖኖ፣ በጂባት፣ በደንዲ፣ በጀልዱ፣ በኤጀሬ፣ በወንጪ፣ በአመያ፣ በአዳኣ፣ በአንቻር እና በአውባሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እየተስተዋለ ስለሆነ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲዩት ይጠቁማል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ኦሞ፣ አማሮ፣ ቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the coming day, the weather conditions favourable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the areas benefiting from Kiremt rains. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benishangul Gumuz region Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones From South Ethiopia region, Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Sit and Fafen zones of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Humera, Welkait, Maykadira, Tsegede, Dansha, Shire Endesilase, Shiraro, Adwa, Aksum, Abergele, Sahartisamre, Atsebi, Dalifagi, Chifra, Dalol, Berahale, Abiala, Debark, Metema, Fogera, Farta, Laigaint, Simada, Pawe, Jawi, Dangila, Bulen, Dangur, Wemberima, Sekela, Mecha, Motta, Sekota, Zikuala, Lasta, Dawunt, Wadila, Mekdella, Kelela, Sayint, Wegid, Desie, Merabete, Moretnajru, Antsokia, Mao Komo, Asossa, Abobo, Jore, Gog, Dima, Addis Ababa, Gidami, Gida, Sibusire, Dera, Degam, Jida, Yaya Gulele, Nono, Jibat, Dendi, Jeldu, Ejere, Wenchi, Ameya, Adaa, Anchar and Awubare will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute suggests that the community should take the necessary precautions as heavy rains are being observed repeatedly in various parts of the country. On the other hand, south Omo, Amaro, Borena and east Bale zones will receive light rainfall at a few places.