Daily Weather Report 24 Aug 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሙ በሆኑት የትግራይ፤ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና ቡለን ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ኑዌር ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ስልጤ እና ጉራጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአፅቢ፣ በሻሁራ፣ በመተከል፣ በላሬ፣ በሳዉላ፣ በወላይታ፣ በፊቼ፣ በኢጃጂ፣ በገለምሶ፣ በቁሉቢ፣ በላንጌ እና በካራሚሌ፣ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rain benefiting areas of Tigray, Amhara, Benishangul-Gumuz, Gambella, Oromia, Afar, Southwest, Central and Southern Ethiopia, as well as eastern parts of the country had strong cloud cover and accumulation. In association with this, northwest, central, south, southeast and east Tigray zones; north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra Zones; from Afar region Awsi and Gabi Zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel and Bullen Zones; from Gambella region Agnwuak and Nuer zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horogudru, West and East Wellga, north, west, southwest and east Shewa, west Guji, Arsi, west and east Hararge Zones; Addis Ababa, Dire Dawa, Harar; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dauro zones; from Central Ethiopia region Hadia, Silte and Gurage zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo and South Omo zones, and the zones of Sidama region received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy amounts of rainfall of more than 30 mm were recorded in Atsibi, Shahura, Metekel, Lare, Sawla, Wolaita, Fiche, Ejaji, Gemelso, Kulubi, Lange and Karamile.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳሊፋጊ፤ በቡለን፣ በዳንጉር፣ በፓዌ፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በሰከላ፣ በአለፋ፣ በፎገራ፣ በሞጣ፣ በወምበርማ፣ በደላንታ፣ በዋድላ እና በመቅደላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተለይም ከዕለት ወደ ዕለት ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ በአዋሽ፤ በአባይ እና ባበሮ ተፋሰሶች ላይ እየተስተዋለ ስለሆነ ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡ በሌላ በኩል በጎፋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አዉሲ እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ጃራር ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the forecast information indicates there will be strong and widespread cloud coverage and accumulation over the parts of the country that benefit from the Kiremt rains. In line with this, from the Tigray region the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, Bale, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region, Wolaita and Gedeo Zones; all zones of Sidama region and from the Somali region Siti zone will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Dalifagi; Bulen, Dangur, Pawe, Jawi, Dangila, Sekela, Alefa, Fogera, Mota, Wemberima, Delanta, Wadila and Makdela will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Especially, the frequent heavy rainfall as it is being observed in Awash, Abay and Baro basins, the Ethiopian Meteorological Institute suggests that the community and concerned bodies should take necessary precautions. On the other hand, Gofa, west and east Hararge, Awusi and from the Somali region Fafen and Jarar zones will receive light rainfall in some places.