Daily Weather Report 24 Aug 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ጉራጌ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎንደር፣ በደብረታቦር፣ በአምደወርቅ፣ በአለም ከተማ እና በቡለን ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, north, west, northeast, central, southwest and eastern parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In association with this, from the Tigray region the northwest, central and southern zones; from the Amhara region north, south and central Gondar, east and west Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Afar region Awusi and Gabi zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa; from the Oromia region of Jimma, Ilubabor Horo Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Hadiya and Gurage zones and from the southern Ethiopia region Wolayta zone received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Gondar, Debre Tabor, Amdework, Alem Ketama and Bullen.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሸ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጌዲኦ እና ጎፋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀገደ፣ በወልቃይት፣ በማይካድራ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ፣ በሽሬ እንዳሥላሴ በሽራሮ፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በአበርገሌ፣ በደባርቅ፣ በመተማ፣ በደብረታቦር፣ በነፋስመዉጫ፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በባህርዳር፣ በሞጣ፣ በአምደወርቅ፣ በሰቆጣ፣ በላስታ፣ በወገዴ፣ በአንጾኪያ፣ በሚንጃርሸንኮራ፣ በደብረብርሀን፣ በቡለን፣ በወንበራ፣ በካማሽ፣ በአይራ፣ በጉሊሶ፣ በጃርሶ፣ በአልጌ፣ በሳሲጋ፣ በነቀምቴ፣ በጊምቢ፣ በነጆ፣ በበደሌ፣ በሰተማ፣ በአመያ፣ በወንጪ፣ በወሊሶ፣ በአሰኮ እና በአንቻር በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ጋሞ፣ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ኖጎብ እና ቆራሔ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the western half, northeastern, southern, central and eastern parts of the country. In line with this, from the Tigray region the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, Bale and east Bale, west and east Hararge, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones and from the southern Ethiopia region Wolaita, Gedeo and Gofa zones; all zones of Sidama region and Sit and Fafen Zones of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Tsegede, Welkait, Maykadira, Dansha, Humera, Shire, Endesilase, Shiraro, Adwa, Aksum, Abergele, Debark, Metema, Debretabor, Nefasmewucha, Dangila, Chagni, Bahir Dar, Motta, Amdework, Sekota, Lasta, wegede, Antsokia, Minjarshenkora, Debre Drehan , Bulen, Wenbera, Kamash, Aira, Guliso, Jarso, Alge, Sasiga, Nekemte, Gimbi, Nedjo, Bedele, Setema, Ameya, Wenchi, Weliso, Aseko and Anchar will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Gamo, Borena, west Guji and Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Nogob and Korahe zones of Somali region will receive light rainfall in some places.