Daily Weather Report 24 Aug 11

Weather Summary for previous day

Aug. 10, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ ፣ በመካከለኛው ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የ ምዕራብ ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂ፣ አርሲ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነቀምቴ፣ በጉንዶ መስቀል፣ በማጀቴ፣ በላንጌ፣ ግራዋ እና በቁልቢ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover and accumulation over the North-West, North-East, Central, West, South and East parts of the country. In connection with this, the West, Northwest, Central, South and East zones of the Tigray region; Central Gondar, East and West Gojam, North and South Wolo, North Showa and Waghemra zones from Amhara Region; Kamash zone from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor Horogudru, Kelem, West and East Wollega, East Showa, Guji, RC and West Hararge zones; Addis Ababa; Bench Sheko and Sheka zones from Southwest Ethiopia region; From Wolayta Zone of Southern Ethiopia Region; From the central region of Ethiopia, Hadiya zone; From the central region of Ethiopia, Hadiya zone; The Wolayita, Gofa and South Omo zones of Southern Ethiopia region, and the Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30mm of heavy rainfall was recorded in Nekemte, Gundo Cross, Majete, Lange, Garwa and Kulbi.

Weather Forecast for next day

Aug. 12, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና፣ ምስራቅ ፣ ሆሮጉድሩ እና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ማይካድራ፣ ዳንሻ ፣ ሁመራ፣ሽሬ እንዳሥላሴ ፣ ሽራሮ፣ አድዋ ፣አክሱም፣ማይጨው ፣ጨርጨር፣ ፅፅቃ፣ ሰቆጣ፣ ዋግኸምራ፣ አምደወርቅ፣ ላሊበላ፣ መርሳ ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ ፣ ሻምቡ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ጅባት ፣ መቱ እና ቡሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ድሬዳዋ፤ ሐረር፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Our numerical forecast indicates that favorable weather events for the formation of winter rains will continue to strengthen. In addition, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi Zone, North and South Wolo, Oromo Ethnic Special Zone, North Showa and Waghemra Zones from Amhara Region; From the Afar region, the zones of Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati; Plantation, Asosa, Mao Como and Kamash zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, East, Horogudru and Kelem Wollega, South West, East, North and West Showa, Guji, Bale, Arsi and West Arsi zones; Addis Ababa; Anuwak and Majang Zones of Gambella Region; Bench Sheko, Sheka, Kefa and Konta zones from Southwest Ethiopia region; From the central Ethiopian region of Gurage, Silte, Halaba, Hadya, Yem Special Zone and Tambaro Zones; All zones of Sidama region and City zone of Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Maikadra, Dansha, Humera, Shire Endasilase, Shiraro, Adwa, Aksum, Maichew, Chercher, Tsitsaka, Sekota, Waghemra, Amdework, Lalibela, Mersa, Horogudru Welega, Shambu, Jimma, Ambo, Jibat, Metu and Bure within 24 hours from 30 They will have heavy rainfall of more than mm. On the other hand, Dredawa; Harar, West and East Hararge zones will receive light rainfall at few places.