Daily Weather Report 24 Aug 10

Weather Summary for previous day

Aug. 9, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ ፣ በመካከለኛው ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የ ምዕራብ ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ከአፋር ክልል ፋንቲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአፅቢ፣ በላሊበላ፣ በአዳማ፣ በሳዉላ፣ ማጀቴ እና በአለምከተማ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover and accumulation over the North-West, North-East, Central, South and East parts of the country. In connection with this, the West, Northwest, Central, South and East zones of the Tigray region; From the Central Gondar, East and West Gojam, North and South Wolo, North Showa and Waghemra zones of Amhara region; Fanti zone from Afar region; Kamash and Asosa zones of Benshangul Gumuz region; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor Horogudru, Kelem, West and East Wollega, East Showa, Guji and West Guji, Arsi and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Bench Sheko and Sheka zones from Southwest Ethiopia region; From the central region of Ethiopia, Hadiya zone; from Southern Ethiopia region Wolayita, Gofa and South Omo zones, and the Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded in Atsibi, Lalibela, Adama, Sawula, Majete and Alem ketema.

Weather Forecast for next day

Aug. 11, 2024

በነገው ዕለት በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፅፅቃ፣ማይጨው ፣ ጨርጨር መተከል፣ ቡለን ፣ አይከል፣ ዳንግላ፣ ላሊበላ፣ መርሳ ፣ ቆቦ፣ መካነ ሰላም፣ ወረኢሉ ፣ ደሴ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ ፣ ጃርሶ፣ ያያ ጉለሌ እና ፍቼ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ድሬዳዋ፤ ሐረር፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud cover and accumulation over the parts of the country benefiting from winter rains. In addition, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi Zone, North and South Wolo, Oromo Ethnic Special Zone, North Showa and Waghemra Zones from Amhara Region; From the Afar region, the zones of Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati; Plantation Zones from Benshangul Gumuz Region, Mao Komo and Kamash; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and East Welega, Horogudru Welega, Kelem Welega, Southwest, East, North and West Showa, Guji, Bale, Arsi and West Arsi zones; Addis Ababa; Anuwak and Majang Zones of Gambella Region; Bench Sheko, Sheka, Kefa and Konta zones from Southwest Ethiopia region; From the central Ethiopian region of Gurage, Silte, Halaba, Hadya, Yem Special Zone and Tambaro Zones; All zones of Sidama region and City zone of Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Tsitsaka, Maichiw, cherecher, Bulen, Aykel, Dangla, Lalibela, Mersa, Kobo, Mekene Selam, Wareilu, Dese, Horogudru Welega, Jarso, Yaya Gulele and Fiche will receive heavy rainfall of over 30 mm in 24 hours. . On the other hand, Dire Dawa; Harar, East Hararge zones will receive light rainfall at few places.