Daily Weather Report 24 Aug 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ አርሲ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአምደወርቅ፣ በጊምቢ፣ በቴፒ፣ በሳዉላ እና በብላቴ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had strong cloud coverage and accumulation over the north, west, and south, central, northeast and east parts of the country. In association with this, from the Tigray region the northwest, central, south and east zones; from the Amhara region central Gondar, east and west Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Benshangul Gumuz region Kamash and Asosa zone; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, west and east Wellega, east Shewa, Guji and west Guji, Borena, Arsi and east Hararge zones; Addis Ababa; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko and Sheka zones; from the central region of Ethiopia Hadiya zone; from the southern Ethiopia region Wolaita, Gofa and south Omo zones of, and the Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Amdework, Gimbi, Tepi, Sawula and Bilate.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአበርገሌ፣ በደባርቅ፣ በላይጋይንት፣ በላስታ፣ በዳዉንት፣ በከለላ፣ በጉባላፍቶ፣ በሰቆጣ፣ በሞጣ፣ በዳንግላ፣ በሾላገበያ፣ በደብረብርሀን፣ በቡለን፣ በወንበራ፣ በጊምቢ፣ በነጆ፣ በበደሌ፣ በአዳአ፣ በሙኔሳ፣ በአመያ እና በጠና በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ቦረና፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ድሬዳዋ፤ ሐረር እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር እና ኤሬር ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the coming day, the numerical weather prediction indicates that weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen in the areas of the country that benefit from Kiremt rains. In line with this, from the Tigray region the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati; from the Benshangul Gumuz region Metekel, Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, Bale, west Hararge, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; from the Gambella region Agnuwak and Majang Zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from south Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Basketo and Gedeo zones; All zones of Sidama region and Siti zone of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Abergele, Debark, Laigaint, Lasta, Dawunt, Kelela, Gubalafto, Sekota, Motta, Dangila, Sholagebeya, Debrebrehan, Bullen, Wanbera, Gimbi, Nedjo, Bedele, Ada’a, Munesa, Ameya and Tena will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Gamo, south Omo, Borena, east Bale, west Guji, east Hararge, Dire Dawa; Harar and Fafen, Jarar and Erer zones of Somali region will receive light rainfall in some places.