Daily Weather Report 24 Aug 08

Weather Summary for previous day

Aug. 7, 2024

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛዎቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ሀቲ እና አዉሲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ስልጤ፣ ሀላባ እና ጉራጌ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የቆራሔ ዞን፤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በማጀቴ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage and accumulation across most parts of the Kiremt rainfall benefiting areas of the country. In association with this, from the Tigray region southeast and central zones; from the Amhara region north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Hati and Awusi zones; from the Oromia region Jimma, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, west Guji, Borena, Bale, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko and Konta Zones; from the central Ethiopian region Hadiya, Silte, Halaba and Gurage zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the south Ethiopia region Wolaita and south Omo Zones; Sidama region zones and Korahe Zone from Somali region received light to moderate rainfall; heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Majete.

Weather Forecast for next day

Aug. 9, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሸ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአድዋ፣ በአበርገሌ፣ በእንደርታ፣ በኦፍላ፣ በአዲግራት፣ በፍሬወይኒ፣ በአፅቢ፣ በደባርቅ፣ በሰቆጣ፣ በቆቦ፣ በጉባላፍቶ፣ በደሴ፣ በባቲ፣ በአዉራ፣ በጭፍራ፣ በተላላክ፣ በገዋኔ፣ በአሳይታ፣ በኖኖ፣ በአመያ፣ በወንጪ እና በሊሙሴቃ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አኙዋክ፣ ጋሞ፣ አማሮ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the western half, northeast, south, central and eastern parts of the country. In line with this, from the Tigray region western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi Zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region of Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from Benshangul Gumuz region Metekel, Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horro Guduruu Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji and west Guji, Bale, west Hararge, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the Gambella region Majang Zone; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from south Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Basketo and Gedeo zones; All zones of Sidama region and Siti zone of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Adwa, Abergele, Enderta, Ofila, Adigrat, Freweyn, Atsebi, Debark, Sekota, Kobo, Gubalafto, Dessie, Bati, Awura, Chifra, Talalak, Gewane, Asayita, Nono, Ameya, Wenchi and Limuseka will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Agnuwak, Gamo, Amaro, east Bale, east Hararge and Fafen zone of Somali region will receive light rainfall in some places.