Daily Weather Report 24 Aug 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢ ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ጉራጌ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ ሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, north, northeast, southwest, south and east parts of the country had cloud coverage and accumulation. In association to this, from Tigray the region northwest, central, south and east zones; from the Amhara region north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Gabi zone; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru and east Wellega, west and east Shewa, west Guji, Bale, east Hararge, Arsi and Arsi west zones; Addis Ababa; Harar; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko and Sheka zones; from the central Ethiopia region Hadiya and Gurage zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel zone; from the south Ethiopia region Wolaita, Gamo, Konso and south Omo zones, all zones of Sidama region and Fafen zone from the Somali region received light to moderate rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ አማሮ፣ ጌዲኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀገደ፣ በሽሬ እንዳሥላሴ፣ በሽራሮ፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት፣ በፍሬወይኒ፣ በአፅቢ፣ በአበርገሌ፣ በሰቆጣ፣ በቆቦ፣ በላሊበላ እና በደሴ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ካማሽ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ቤንች ሸኮ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the coming day, there will be strong and widespread cloud coverage and accumulation over the northwest, northeast, central, southwest, south and east parts of the country. In line with this, from the Tigray region western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region the Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel and Asosa zones; from the Oromia region Jimma, east Wellega, Horo Guduru Wellega, southwest and east Shewa, Guji and west Guji, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi zones; from the southwest Ethiopia region Konta, west Omo, Dawuro and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Derashe, Amaro, Gedeo and south Omo zones; All zones of Sidama region and Fafen zone of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Tsegede, Shire Endesilase, Shiraro, Adwa, Axum, Adigrat, Freweyn, Atsebi, Abergele, Sekota, Kobo, Lalibela and Dessie will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Kamash, west Wellega, north and west Shewa, Borena, west and east Hararge, Addis Ababa, Dire Dawa, Harar, Bench Sheko, Burji, Konso and the Fafen zone of the Somali region will receive light rainfall in some places.