Daily Weather Report 24 Aug 06

Weather Summary for previous day

Aug. 5, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ፣ ሀላባ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ጋሞ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በመቀሌ፣ በአይከል፣ በደብረታቦር፣ በባህርዳር፣ በአምባማሪያም፣ በጨፋ፣ በጭፍራ፣ በማጀቴ፣ በአሶሳ እና በአርጆ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, over the north, west, northeast, south and east parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In association with this, from the Tigray region northwest, central, south and east zones, the northwest, central, south and east zones; from the Amhara region north, south and central Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, east and west Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, Bale, west and east Hararge, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko and Konta Zones; from the central Ethiopian region Hadiya, Gurage, Halaba and Silte zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the southern Ethiopia region Wolaita, Gofa and Gamo zones and from the Gambella region Agnuwak zone of received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over in Mekelle, Ayikel, Debretabor, Bahirdar, Ambamariam, Chifra, Majete, Asossa and Arjo.

Weather Forecast for next day

Aug. 7, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ ሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ፣ ሊበን እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀገደ፣ በሽሬ እንዳሥላሴ፣ በሽራሮ፣ በአድዋ፣ በአክሱም እና በማይፀብሪ፤ በደባርቅ፣ በአይከል፣ በመተማ፣ በዋግኸምራ፣ በቆቦ፣ በላሊበላ፣ በደሴ፣ በጉባ፣ በጋምቤላ፣ በማጃንግ፣ በቡሬ፣ በደንብዶሎ፣ በመቱ፣ በሸካ እና በከፋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ድሬዳዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ እና ቆራሔ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, For the coming day, the weather conditions that favorable conditions for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over the northwest, west, northeast, central, southwest, south and east regions of the country. In line with this, from the Tigray region western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region the Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benshangul Gumuz region Metekel, Asosa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east and west Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, Bale and east Bale, west and east Hararge, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Itang, Nuwer and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Konta, west Omo, Dawuro and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopian region Wolayta, Gofa, and Basketo zones; All zones of Sidama region and the zones of Siti, Dawa, Liben and Erer of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, in Tsegede, Shire Endesilase, Shiraro, Adwa, Axum and Maitsebri; Debark, Ayikel, Metema, Waghemra, Kobo, Lalibela, Desie, Guba, Gambella, Majang, Bure, Denbidollo, Mettu, Sheka and Kefa will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand Dire Dawa, west Guji, Borena and Fafen, Jarar, Nogob, Afder, Shebelle and Korahe zones of Somali region will receive light rainfall in some places.