Daily Weather Report 24 Aug 02

Weather Summary for previous day

Aug. 1, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ጠንካራ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ እና ወላይታ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በስንቃጣ (በፍሬወይኒ)፣ በአፅቢ፣ በደባርቅ፣ በአምደወርቅ፣ በላይበር፣ በየትኖራ፣ በአሶሳ፣ በድሬዳዋ እና በአቦምሳ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, north, northeast, west, southwest, south, central and eastern parts of the country had strong cloud coverage and accumulation. In this regard, from the Tigray region northwest, central, southeast, south and east zones; from Amhara region north, south and central Gondar, east and west Gojam, Awi, north and south Wallo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Borena, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the central Ethiopian region Hadiya, Halaba and Silte zones; from the south west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko and Dawuro zones; from the South Ethiopia region Gofa, Gamo and Wolayta zones; from Benshangul Gumuz region Asosa zone; from the Gambella region Agnuwak zone; from the Afar region Gabi and Hati zones and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Senkata (Freweyini), Atesbi, Debark, Amdework, Laiber, Yetnora, Asossa, Dire Dawa and Abomsa.

Weather Forecast for next day

Aug. 3, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳዉሮ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደሴ፣ በመቅደላ እና ጨፋ፤ በቀወት፣ በምንጃርሸንኮራ እና በበረሐት፤ በጋብላሉ፤ በጅባት፣ በጂዳ፤ በአመያ፤ በፈንታሌ፤ በነቀምቴ እና በጎቡሰዮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ኦሞ፣ በጌዲኦ፣ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ በቦረና፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ኤሬር፣ ሊበን እና አፈደር ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will continue to strengthen over northwest, west, northeast, south, central and eastern parts of the country. In line with this, from the Tigray region western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojam, Awi, north and south Wallo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hati zones; from the Benshangul Gumuz region Asossa, Mao Komo and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east and west Wellega, Horo Guduru Wellega, Kelam Wellega, southwest, east, north and west Shewa, Guji, west Hararge, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Dawuro, Konta and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; All zones of Sidama region; from the southern Ethiopia region Wolaita Zone and from the Somali region the Siti Zone of will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition in Desie, Mekdella and Chafe Donsa; Kewat, Minjarshenkora and Berehat; In Gabilalu, Jibat, Jidda; Fentale, Nekemte and Gobuseyo will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, west Omo, Gedeo, Bale and, east Bale, Borena, east Hararge, Dire Dawa, Harar, and Fafen, Jarar, Korahe, Nogob, Erer, Liban and Afder zones of Somali region receive light rainfall in some places.