Daily Weather Report 23 June 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከአማራ ክልል በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፤ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነቀምቴ እና አከባቢው ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in the North, North East, Central South and South West parts of the country. In connection with this, from Amhara region in West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, North and South Wolo, North Showa and Awi zones; From Oromia region, Ilubabor, Buno Bedele, West, South West, East and North Shewa, East and Horo Gudru Welega, Arsi and West Arsi; Guji and Borena zones; In Addis Ababa. From Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of central Ethiopia region; They received light to moderate rainfall. Also, heavy rainfall was recorded in and around Nekmet.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በሰሜን ምዕራብ፤ በምዕራብ ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ በሐረር፤ በድሬዳዋ፤ በአዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ እና ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሃቲና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ቆራሄ እና ኖጎብ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም በምስራቅ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ እና ጅማ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, In the northwest, which will benefit from Kiremt rains; Our numerical forecast data indicates that there will be strong and widespread cloud cover and accumulation in the western, central, northeastern, southern, southwestern and eastern parts of the country. In connection with this, from the western, central Tigray region; Northwest, Southeast, South and East zones; North, South, West and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, North Showa, Oromia Special Zone and Waghemra Zones from Amhara Region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horo Gudru, Welega, Southwest, North, East and West Showa, Arsi and West Arsi, Guji, Bale and West Hararge zones; in silk In Dire Dawa In Addis Ababa. Planting and foundation zones from Benshangul Gumuz region; From Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; From South Ethiopia Region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo Zones; and from the Afar region of Kilbeti, Awusi, Gabi, Hati and Fanti zones; From the Somali Region, City, Fafen, Jarar, Korahe, and Nogob will have light to moderate rainfall in many places. In addition, East Tigray, West, Central, North and South Gondar, Waghemra, North Wolo and Jimma zones will receive heavy rainfall within 24 hours.