Daily Weather Report 22 June 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፤ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎሬ እና አከባቢው ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in the North, North East, Central South and South West parts of the country. In connection with this, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, North and South Wolo, North Showa and Awi zones of Amhara region; From Oromia Region, Buno Bedele, West, South West, East and North Showa, East and West Hararge, Horo Gudru Welega, Arsi and West Arsi; Guji and Borena zones; In Addis Ababa. Bench Sheko, Fefan, Dawuro zones of Southwest Ethiopia received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall was recorded in Gore and its surroundings.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፤ በምዕራብ ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ፣ መተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ እና ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሃቲና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራር፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ አፍዴር እና ሊበን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጂማ እና አርሲ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, the Weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains in the northwest; They will continue to be stronger in the western, central, northeastern, southern, southwestern and eastern regions of the country. In connection with this, from the western, central Tigray region; Northwest, Southeast, South and East zones; North, South, West and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, North Showa, Oromia Special Zone and Waghemra Zones from Amhara Region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horo Gudru, Welega, Southwest, North, East and West Showa, Arsi and West Arsi, Guji, Bale and West Hararge zones; In Addis Ababa, Kamash, Metekel and Asosa zones of Benshangul Gumuz region; Majang, Anuwak and Itang zones of Gambella region; Sheka, Fefan, Bench Sheko, Dawuro and Konta zones of South West Ethiopia region; From Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; From South Ethiopia Region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo Zones; and from the Afar region of Kilbeti, Awusi, Gabi, Hati and Fanti zones; From the Somali Region, City, Fafen, Erer, Jarar, Korahe, Shebele, Afder and Liben will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, our numerical forecast data indicates that heavy rainfall will occur in Northwest Tigray, West, Central, North and South Gondar, West and East Gojam, Jimma and RC zones within 24 hours.