Daily Weather Report 21 June 2024

Weather Summary for previous day

June 20, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምስራቅ፣ምዕራብና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፤ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን፤ ሐረር፣ ድሬዳዋ እና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቡኢ እና በተርጫ አካባቢዎች ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was cloud cover in the north, west, northeast, east, south and central parts of the country. In connection with this, the central and southern zones of the Tigray region; north and central Gondar, west and east Gojam, north and south Wolo, north Showa and Awi zones of Amhara Region; from the Oromia region, Jimma, Buno Bedele, west, southwest and north Showa, east and west Hararge, east, west and Horo Gudru Wolega, Arsi and west Arsi; Guji and Borena zones; from Southwest Ethiopia Region Dauro zone; from South Ethiopia region, Wolayta zone; from Somali region Fafen zone; Harari, Dredawa and Addis Ababa received light to moderate rainfall whereas Bui and Tercha areas recorded heavy rainfall.

Weather Forecast for next day

June 22, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሰሜን ምዕራብ፤ በምዕራብ ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ፣ መተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌድ ኦ ዞኖች፤ እና ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሃቲና ፋንቲ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጂማ፣ ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the next day, there will be strong and widespread cloud cover over the Kiremt-rainfall benefiting areas of western, central, northeastern, southern and southwestern parts of the country. In association with this, from the Tigray region western, central; northwest, southeast, south and east zones; from Amhara region north, south, west and central Gondar, west and east Gojam, Awi, north and south Wolo, north Showa, Oromia Special zone and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horo Gudru, Welega, southwest, north, east and west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Bale and west Hararge zones; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region Kamash, Metekel and Asosa zones; from Gambella region Majang, Anuwak and Itang zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Kefa, Bench Sheko, Dauro and Konta zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of; All zones of Sidama region; from South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedio zones; and from Afar region, Kilbeti, Ausi, Gabi, Hatina Fanti zones receive light to moderate rainfall in many places. In addition, North and South Gondar, Waghemra, East Welega, Jimma, West and South West Showa and West Arsi zones will receive heavy rainfall within 24 hours.