Daily Weather Report 20 March 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሸፋን ተስተውሎባቸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል በደቡብ ጎንደርና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ምዕራብና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ኮንታ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን እና በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን በጥቂት ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቦባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ 41.6፣ በፉኝዶ 42.8፣ አቦቦ 39.8፣ ላሬ 41.0፤ ሰመራ 37.0፤ ዱብቲ 37.0፤ አዋሽ አርባ 40.0፤ በጎዴ 41.8 እና በቀብሪ ደሃር 36.0 ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ 35-43 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday Cloud cover was observed in the north-west, north-east, west, south, south-west and central areas of the country. Along with this, from Amhara region in South Gondar and South Wolo zones; From Ilubabor, Jimma, West and Horo Gudru Wollega zones of Oromia region; From the South West region of Ethiopia, Kefa, Sheka, Bench Sheko and Konta zones; from Southern Ethiopia region Gamo zone and Gambella region Anuwak zone Light to heavy rains have been recorded in a few places. On the other hand, Gambella 41.6, Fugnedo 42.8, Abobo 39.8, Lare 41.0; Semera 37.0; Dubti 37.0; Awash Arba 40.0, Gode 41.8 and 36.0 at Kabri Dehar 36.0 the maximum temperature of the day was recorded at 35-43 degree Celsius
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ስለሆነም በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል በምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሺና አሶሳ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ፣ ኑኤር፣ ማጃንግና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳዉሮና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን በተጨማሪም በአሶሳ እና ቄለም ወለጋ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በጋምቤላ፣ ላሬ፣ አቦቦ፤ መተማ፣ ቋራ፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ ጎዴ እና ቀብሪ ደሃር አከባቢዎች ላይ ከ38-42 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ ይጠበቃል፡፡
Tomorrow the weather events favorable for the formation of Belg rains will intensify. Hence, there will be strong cloud cover and accumulation over North West, South, South West and West parts of the country. Along with this, in the west, north and west zones of the Tigray region; West and central Gondar, Awi and West Gojam zones of Amhara region; Ilubabor, Buno Dele, Jimma, Kelem, Horo Gudru, West and East Welega and zones from the Oromia region; from Benshangul Gumuz Region, Mao Komo, Kamashi and Asosa Zones, from Gambella Region Itang, Nuer, Majang and Anuwak Zones From South West Ethiopia region, Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawero and West Omo zones And the zones of Sidama region will have light to moderate rainfall in many places and heavy rainfall in few places in Asosa and Kelem Wollega. On the other hand, the maximum temperature of the day in Gambella, Lare, Abobo; Metema, Qara, Dubti, Semera, Gode and Kebri Dehar areas are expected to record 38-42 degrees Celsius.