Daily Weather Report 20 June 2024

Weather Summary for previous day

June 19, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊና ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምስራቅና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ሐረር እና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በተጨማሪም በደብረ ማርቆስ እና አከባቢው ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover in the north, northeast, southwest, south and central parts of the country. In connection with this, the central and southern zones of the Tigray region; West, North, South and Central and Gondar, West and East Gojam, North and South Wolo, North Showa and Awi zones of Amhara region; From the Oromia region of Jimma, Buno Bedele, West, South West and North Showa, East and West Hararge, East and Horo Gudru Wollega, Arsi West and Arsi and Guji and West Guji zones; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia; Harar and Addis Ababa received light to moderate rainfall, while Debre Markos recorded heavy rainfall.

Weather Forecast for next day

June 21, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ፣ ማኦ ኮሞና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ጌድኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል ፋፈን፣ ኤረርና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow the Weather conditions favorable for the formation of Kiremt rains will continue to intensify over the western, central, southern, north eastern and eastern parts of the country. Along with this, from the central region of Tigray; North West, South East and East Zones; West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, North Showa and Waghemra zones of Amhara Region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horo Gudru Welega, West, Southwest, North and East Showa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; Addis Ababa; Asosa, Mao Komo and Kamash zones of Benshangul Gumuz region; Majang, Anuwak and Itang zones of Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Dawuro, Konta and Kefa zones of South West Ethiopia region; From Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; The Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro and Gedeo zones of Southern Ethiopia region and Fafen, Erer and Jarar zones of Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, forecast data indicates that there will be heavy rainfall in a few zones of West and East Gojam, West, South West Showa and West Arsi.