Daily Weather Report 19 June 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ ፣በደቡብ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከአማራ ክልል ሰሜን እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሀረርጌ እና ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ እና ከፋ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ እና ሀላባ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልልል ፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በተጨማሪም በጅማ እና በግራዋ አከባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the northwest, west, southwest, southern, eastern, and central parts of the country. In this regard, from Amhara region north and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north Shewa, and Waghemra zones; Oromia Region: Jimma, Buno Bedele, southwest, east Shewa, west, east, Kelem and Horo Gudru Wolga, Arsi and west Arsi, Bale, east Hararge, and Guji zones; Addis Ababa; from the Southwest Ethiopia region, Sheka, Bench Sheko, Dawro, and Kefa zones; all zones of the Sidama region; from the Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadiya, and Halaba zones; Wolayte and Gedeo zones of the Southern Ethiopia Region; and from the Somali region, Fafen Zone had received light to moderate amounts of rain. In addition, heavy rainfall was recorded in Jimma and Grawa areas.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ጌድኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል ፋፈንና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the weather events favorable for rainfall will intensify in the western half, central, southern, northeast and eastern parts of the country. In association with this, the west, central, northwest, southeast and east zones of the Tigray region; from Amhara region north, south and central Gondar of, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Oromia region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horo Gudru Wolega, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and, West Guji, Bale, Borena and east Hararge zones; Addis Ababa; Benishangul-Gumuz region, Asossa and Kamash zones; Gambella region Majang zone; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Dawro, Konta and Kefa zones; from Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kembata and Tembaro zones; All zones of Sidama region; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Baseketo, Burji, Amaro and Gideo zones and from Somali region Fafen and Jarrar zones light to moderate amounts of rain will receive in many places. In addition, the northwest and central Tigray, west Arsi and west Shewa zones will receive heavy amounts of rainfall within 24 hours.