Daily Weather Report 18 June 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ ፣በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከአማራ ክልል ምዕራብ፣ ሰሜን እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ፤በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ሐረር እና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በጉብይሬ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in the North-West, West, South-West, South and Central parts of the country. In connection with this, from Amhara region West, North and Central Gondar, West and East Gojam and Awi zones; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, Southwest, East Showa, East, West, East, Kelem and Horo Gudru Welega, Arsi and West Arsi and Guji and West Guji zones; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia; In all the zones of the Sidama region; Harar and Addis Ababa received light to moderate rainfall while Gubyre recorded heavy rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሰሜን ምዕራብ፤ በምዕራብ ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ አማሮ እና ጌድኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ማዕከላዊ ጎንደር እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the coming day, In the northwest, which will benefit from Kiremt rains; There will be strong and widespread cloud cover over the western, central, southern and southwestern parts of the country. Along with this, from the western, central Tigray region; North West, South East and East Zones; North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, North Showa and Waghemra zones of Amhara Region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East and Horo Gudru Wollega, Southwest, North and West Showa, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale zones; In Addis Ababa. Kamash Zone of Benshangul Gumuz Region; From Majang Zone of Gambella Region; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia; From Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; The Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro and Gedeo zones of Southern Ethiopia will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Northwest Tigray, Central Gondar and West Shewa zones will receive heavy rainfall within 24 hours.