Daily Weather Report 17 June 2024

Weather Summary for previous day

June 16, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ እና ጉጂ ዞኖች እና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው። ከባድ ዝናብ ከተመዘገበባቸው መካከል በአሶሳ፣ ጊምቢ፣ አይራ እና ሽሬ እንዳስላሌ ይጠቀሳሉ፡፡

Yesterday, they had strong cloud cover and accumulation in the northwest, west, south and central parts of the country. In connection with this, from the western zone of the Tigray region; North and South Gondar, West and East Gojam, Awi and North Showa zones of Amhara Region; From Oromia region, Ilubabor, Buno Bedele, West, Southwest, East Showa, East, West, Kelem, Horo Gudru, Welega and Guji zones and Addis Ababa had light to heavy rain. Heavy rains were recorded in Asosa, Gimbi, Aira and Shire Endasilase.

Weather Forecast for next day

June 18, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ አማሮ እና ጌድኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

For the Coming day there will be strong cloud cover and accumulation over the western, central, southern and eastern parts of the country, which will benefit from Kiremt rains. Along with this, from the western, central Tigray region; North West, South East and East Zones; North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, South Wolo and Waghemra zones from Amhara Region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Horo Gudruna, Kelem Wollega, Southwest, North and West Showa, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale zones; In Addis Ababa. Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; from Itang, Anuwak and Majang zones of Gambella region; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia region; From Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; The Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro and Gedeo zones of Southern Ethiopia will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, our numerical forecast data indicates that West and Central Tigray, Central and West Gondar, West Gojam, Awi, West Shewa and Horo Gudru Welega zones will have more than 30 mm of heavy rain in 24 hours.