Daily Weather Report 14 June 2024

Weather Summary for previous day

June 13, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ፣ ጉጅ እና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያና ሀላባ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ቡርጅ፣ ጌዲወ፣ እና ወላይታ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን እና ሀረሪ ክልል ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው። በተጨማሪም በአለም ተፈሪ እና አካባቢው ላይ ደግሞ ከ30 ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud cover and accumulation over the northern, west, southern, central and eastern areas of the country. In this regard, the northwest and central zones of the Tigray region, north and south Gondar of Amhara region, west and east Gojjam, Awi and north Shewa zones; Oromia Region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west, southwest, east and north Shewa, east, west, Kelem and Horo Gudru Wolga, Arsi and west Arsi, Guj and east Hararge zones; Addis Ababa; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa and Dauro zones; from the Central Ethiopia Region of Gurage, Silte, Hadiya and Halaba zones and from southern Ethiopia region Gamo, Gofa, Konso, Burj, Gediwo, and Wolayta zones; from Gambella region Anwuak zone and Harari region had light to heavy amounts of rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded at Alemteferi and surrounding areas.

Weather Forecast for next day

June 15, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ማረቆ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ አማሮ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ድሬዳዋ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምዕራብ ትግራይ፣ ማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, Weather events favorable for Kiremt rainfall will intensify over the west, central, south, and eastern parts of the country. In association with this, the west, central, northwest, southeast and east zones of Tigray region; from Amhara region north, west, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, south Wollo and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Horo Gudrun and Kelem Wolga, southwest, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Benishangul-Gumuz region: Metekel, Assosa, Kamash and Maokomo zones; from Gambella region Itang, Anuwak and Majang zones; from the Southwest Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and west Omo zones; Central Ethiopia Region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Mareko, Kembata and Tembaro zones; all zones of Sidama region; from South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Baseket, Amaro and Gedeo zones of the; from the Somali region, Siti and Fafen zones and Dire Dawa receive light to moderate amount of rainfall in most of their places. In addition, west Tigray, central and west Gondar, west Gojjam, Awi and east Wolga zones will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.