Daily Weather Report 13 June 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ እና የተጠናከረ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ከፋና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያና ሀላባ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ ዞኖች ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በጊምቢ እና አካባቢው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was widespread and concentrated cloud cover and accumulation over the western half, south, north, central and northeastern areas of the country. At the same time, the northwest and central zones of Tigray region, from Amhara region, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, south and north Wollo and north Shewa zones; Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west, southwest, east and north Shewa, east, west, Kelem and Horo Gudru Wolga, Arsi and west Arsi, Guj and west Guj zones; Addis Ababa; from southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, West Omo, Kefa and Dauro Zones; Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadiya and Halaba zones; from Gambella region Anuwak zone; from Benishangul-Gumuz region Assosa zone and from Southern Ethiopia region Gamo, Gofa, South Omo and Wolayta zones had light to heavy amounts of rain. Heavy rains were recorded at Gimbi and surrounding areas.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኑዌር፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ማረቆ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ቡርጅ፣ አማሮ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲና ፋፈን ዞኖች፤ ሐረሪ እና ድሬዳዋ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (ከ1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የሰሜንም ዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ካማሺ፣ አሶሳ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖበደሌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be strong and widespread cloud cover and accumulation over the western half, central, southern, northeast and eastern parts of the country. At the same time, the west, central, northwest, southern, southeast and east zones of the Tigray region; north, west, south and central Gondar of the Amhara region; west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo and Waghemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Horo Gudrun and Kelem Wolga, southwest, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Gujina west Guji, Bale, west and east Hararge Zones; Addis Ababa; Benishangul-Gumuz region: Metekel, Assosa, Kamash and Maokomo zones; from Gambella region Nuer, Itang, Anuwak and Majang zones; from the Southwest Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and west Omo zones; Central Ethiopia Region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Mareko, Kembata and Tembaro zones; all zones of Sidama region; from Southwest Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Baseket, Burj, Amaro and Gedeo zones of the; from the Somali region, Siti and Fafen zones; Harari and Dire Dawa receive light to moderate (1-29 mm) amounts in most of their places. In addition, northern and central Tigray, central and southern Gondar, west Gojjam, Awi, Kamashi, Assossa, east and west Wolga, Ilubabor and Bunodele zones will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.