Daily Weather Report 12 June 2024

Weather Summary for previous day

June 11, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው። በመሆኑም ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያና ሀላባ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ ዞኖች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ ዝናብ ከተመዘገበባቸው ጣቢያዎች መካከልም አዲስ አበባ፣ ጊምቢ እና አይራ ይጠቀሳሉ፡፡

Yesterday, there was strong cloud cover and accumulation over parts of the west, south, central, and northeast of the country. Thus, light to heavy amounts of rainfall were recorded from the North, South, and Central Gondar of Amhara Region, West and East Gojjam, Awi, South Wollo and North Shewa zones, Oromia Region, Jimma, West, Southwest, East and North Shewa, East, West and Horo Gudru Wolga and West Guj Zones, Addis Ababa; Sheka, Bench Sheko, Fana Dauro Zones, Central Ethiopia Region, Gurage, Silte, Hadiya and Halaba zones, and South Omo and Wolayta zones of the Southern Ethiopia Region. Among the stations above 30 mm, heavy amounts of rain were recorded in Addis Ababa, Gimbi and Aira.

Weather Forecast for next day

June 13, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኑዌር፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ማረቆ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን፤ ሐረሪ እና ድሬዳዋ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ትግራይ፤ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፤ መተከል፣ ካማሺ፤ ሆሮ ጉድሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር እና አኙዋክ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be strong and widespread cloud cover and accumulation over the west, central, southern, northeastern, and eastern parts of the country. At the same time, the West, Central, Northwest, South, Southeast and East zones of the Tigray region; North, West, South and Central Gondar of Amhara region, West and East Gojjam, Awi, South Wollo, North Shewa Zone and Waghemra Zones; Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Dele, East, West, Horo Gudrun and Kelem Wolga, Southwest, North, East and West Shewa, Arsina West Arsi, Gujina West Guji, Bale, West and East Hararge Zones; Addis Ababa; from Benishangul-Gumuz region of Metkel, Assossa, Kamash and Maokomo Zones; from Gambella Region Nuer, Itang, Anuwak and Majang Zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and West Omo zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Mareko, Kembatana Tembaro zones; all zones of Sidama region; from Southern Ethiopia region; Somali Region Wolayta and Gideo zones; from Somali region Siti Zone, Harari and Dire Dawa will receive light to moderate amounts of rainfall in many of their locations. Also in western Tigray, west, central, and south Gondar, west Gojjam, Awi, Metekel, Kamashi, Horo Gudru, East and West Wolga, Ilubabor, and Anwuak zones will receive above 30 mm of heavy rain in 24 hours.