Daily Weather Report 11 June 2024

Weather Summary for previous day

June 10, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፣ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያና ሀላባ ዞኖች፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover over the western, central and eastern parts of the country. Therefore, from the Tigray region, the west, central; North West and East Zones; North and Central Gondar, West and East Gojam Zones of Amhara Region; From the Oromia region Jimma, West, Southwest, East and North Showa, East, West and Horo Gudru, Welega and East Hararge zones; Harar, Addis Ababa; From Sheka, Bench Sheko, Kefa Konta zones of Southwest Ethiopia region; From Gurage, Silte, Hadiya and Halaba zones of central Ethiopia region, Asosa zone of Benshangul Gumuz region and Gofa, South Omo and Gedeo zones of southern Ethiopia region; Light to moderate rainfall was recorded.

Weather Forecast for next day

June 12, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ዋግኸምራ፣ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ማረቆ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ አውሲ፣ ጋቢና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን፤ ሐረሪ እና ድሬዳዋ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማዕከላዊና ምስራቅ ትግራይ፣ ሆሮ ጉድሩ ምስራቅና ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ እና በአፋር በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, there will be strong and widespread cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from Kiremt rains. In connection with this, from the western, central Tigray region; Northwest, South, Southeast and East zones; North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, North Showa, Oromia Special Zone and Waghemra, Zones from Amhara Region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Horo Gudruna, Kelem Welega, Southwest, North, East and West Showa, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; Anuwak and Majang Zones of Gambella Region; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and West Omo Zones; From Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Mareko, Kambata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All zones of Sidama region; From South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; Kilbeti, Awusi, Gabi and Fanti zones from the Afar region; From Somali Region City Zone; Harari and Dire Dawa will receive light to moderate rainfall in most of their areas. In addition, Central and Eastern Tigray, Horo Gudru East and Welega, West Showa and Afar will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.