Daily Weather Report 10 June 2024

Weather Summary for previous day

June 9, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። በመሆኑም ከአማራ ክልል የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ሆሮ ጉድሩ ወለጋዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያና ሀላባ ዞኖች፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፣ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአማን ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over the northwest, west, southwest, central, and southern parts of the country. In line with this, north and central Gondar, west and east Gojjam zones of the Amhara region; from Oromia region, Jimma, west, southwest, east and north Shewa, east, west, and Horo Gudru Wolga zones; Addis Ababa; from Southwest Ethiopia region, Sheka, Bench Sheko, Kefa, and Konta zones; from Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadiya, and Halaba zones; Benishangul-Gumuz region; Asosa zone; all zones of Sidama region; and from Southern Ethiopia region, Gofa, South Omo, and Gedeo zones received light to heavy amounts of rain, with above 30 mm of heavy rainfall recorded in Aman.

Weather Forecast for next day

June 11, 2024

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩና እንደሚስፋፉ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ዋግህምራ፣ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ማረቆ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልባቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሃሪና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን፤ ሐረሪ እና ድሬ ዳዋ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ጉራጌ፣ ካማሺ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ቂልባቲ እና አውሲ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the coming day, weather events favorable for rainfall will intensify in the western half, central, southern, northeast and eastern parts of the country. In association with this, the west, central, northwest, south, southeast, and east zones of the Tigray region; from Amhara region north, west, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa, Oromia Special Zone and Waghemra, Zones; from Oromia region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Horo Gudru and Kelem Wolga, Southwest, North, east and west Shewa, Arsi and West Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge Zones; Addis Ababa; Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa, Kamash and Maokomo Zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and west Omo zones; from Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Mareko, Kembatana, Tembaro zones; all zones of Sidama region; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gideo zones; from Afar region Kilbati, Aussi, Gabi, Harina Fanti zones; Somali Region Siti Zone; Harari and Dire Dawa will receive light to moderate amounts of rain at most places. In addition, at a few places of central and northwestern Tigray, north, central and south Gondar, Waghemra, west Gojjam, Awi, Kamashi, Gurage, east Wolga, west and southwest Shewa, Jimma, Buno Bedele, Kilbati and Aussie zones will receive heavy above 30mm amounts of rainfall within 24 hours.