Daily Weather Report 08 April 2024

Weather Summary for previous day

April 7, 2024

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሸፋንና ክምችት ተስተውሎባቸዋል። በመሆኑም ከትግራይ ክልል ምስራቅ፣ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ክልል በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሰሜን(ሰላሌ)፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ሸካ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ እና ሀላባ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ድሬዳዋ እና ከሶማሌ ክልል ሊበን ዞን በብዙ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው፡፡ በተጨማሪም ኮንሶ እና ስሪንቃ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ 38.0፣ ሰመራ 38.8 እና ሸርኮሌ 37.0 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, strong cloud cover and accumulation were observed in the North-East, Central, South-West, South and East regions of our country. Therefore, from the Tigray region east, southeast and south zones; from Amhara Region South and North Wolo, Waghimra and North Showa zones; From Oromia region in Jimma, Ilubabor, North (Salale), West, East and Southwest Showa, West Guji and Borena zones; Addis Ababa; From Gambella Region Itang Zone; from South West Ethiopia region Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, West Omo and Sheka zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya and Halaba zones; From South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, South Omo, Basketo and Gedeo zones; Sidama Region Zones; Dire Dawa and from the Somali region Liban zone had light to moderate rainfall in many places. Konso and Srinaqar also recorded heavy rainfall. On the other hand, in Fugnedo 38.0, Semera 38.8 and Sherkole 37.0, the highest temperature of the day was recorded as degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

April 9, 2024

በነገው ዕለት በልግ ዋናኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ፤ከአፋር ክልል ጋቢ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ሸካ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤በሁሉም ሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን፣ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ቆራሄ እና ዳዋ ዞኖች፤ ድሬዳዋ እና ሐረር በብዙ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን፣ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ከፋ እና ሸካ ዞኖች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover and accumulation in the parts of the country which are the main and second rainy season of Belg. In connection with this, from the Tigray region the west, northwest, central, east, southeast and south zones; From Amhara region Central, North and South Gondar, North and South Wolo, Waghmra, East Gojam and North Showa zones; from Afar region Gabi and Hati zones; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Horo Gudru, Kelem Wollega, Buno Bedele, North, West and South West Showa, Borena, Bale, West RC and West and East Hararge zones; Addis Ababa; Anguwak, from Gambella region Majang and Itang zones; from South West Ethiopia region Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro, West Omo and Sheka zones ; From central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Kambata and Tembaro zones; In all Sidama region zones; From South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso and South Omo zones; From Somali region City, Fafen, Liban, Afder, Shebele, Korahe and Dawa zones; Dire Dawa and Harar will receive light to moderate rainfall at many places. In addition, Central Zone of Tigray Region, North Gondar and North Showa Zones of Amara Region, Bench Sheko, Kefa and Sheka Zones of Southwest Ethiopia will have heavy rain.