
በሚቀጥለው የሜይ የመጨረሻዎቹ አሥራ አንድ ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሰፊ ቦታዎችን ያካተተና የተጠናከረ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተስፋፋ ዝናብ የሚኖር ሲሆን እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ