
በጁላይ ሦስተኛው አሥራ አንድ ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተሻለ ሁኔታ ይጠናከራሉ፡፡ ስለሆነም በአብዛኛዎቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ በመደበኛው ሁኔታ ተጠናክሮ ይጥላል፡፡ በመሆኑም አብዛኛዎቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች የተጠናከረና የተስፋፋ ዝናብ እንደሚያገኙ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚኖረው ተከታታይነት ያለው ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ለወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎረፍ ሊያስከትል ይችላል፡፡