21-31 October 2026

Bulletin

በመጪዎቹ የኦክቶበር ሶስተኛዉ አሥራ አንድ ቀናቶች አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም ከተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከሳምንቱ አጋማሽ ጀምሮ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የጉጂ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡