በሚቀጥሉት የኦክቶበር ሶስተኛዉ አሥራ አንድ ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም የተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረና የምስራቅ ቦረና፣ የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡