21-31 May 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚኖሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አከባቢዎች ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ (ከ1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በጥቂት የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡