21-31 March 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት ቀናቶች ለበልግ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከዕለት ወደ ዕለት ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፣ የስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች፣ የመካከለኛው፣ የሰሜን ምስራቅ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ ገፅታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በደቡብ፣ መካከለኛዉ፣ ምስራቅና እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡