በሚቀጥሉት የጃንዋሪ አስራ አንድ ቀናት በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የበጋው ደረቅ፣ ጸሀያማውና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል። በሌላ በኩል ቀስ በቀስ በስምጥ ሸለቆ እና አዋሳኝ አካባቢዎች፣ የመካከለኛውና የደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ላይ መጠነኛ የደመና ሽፋን መጨመር ሲሆንና፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይም አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡