በሚቀጥሉት የዲሴምበር ሶስተኛዉ አሥራ አንድ ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች በተለይም በመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የደቡብ ኦሮሚያ፤ ሲዳማ ክልል፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ እና የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡