በሚቀጥሉት ቀናት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀጣይነት ይኖራቸዋል ፡፡ በተጨማሪም በፀኃይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በተለይም በደቡብ ምዕራብና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተስፋፋና ሰፊ ቦታዎችን የሚያካትት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል ፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛዉ፣ በምስራቅ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡