
በመጪዎቹ የኤፕሪል ሶስተኛዉ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በተለይም የምድር ወገብን አርጦ ወደ ሀገራችን የሚገባው ዕርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተሻለ የደመናና የዝናብ ሥርጭት በደቡባዊው አጋማሽ፤ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት እንደሚኖራቸዉ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡