21-30 November 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት የኖቬምበር ሶስተኛዉ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት አከባቢዎች ላይ በሂደት እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ጉጂ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ በመጠንም እና በስርጭት የተሻለ ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡