በሚቀጥሉት የኖቬምበር የሶስተኛዉ አሥር ቀናት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በጥቂት የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ በአግባቡ በመሰብሰብ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መቀነስ ያስፈልጋል ፡፡